የአበባ ሥዕል ሽያጭ ባለሙያ

Position:

Organization: HaHuJobs

Not Specified

የሥራው ማጠቃለያ፦

ድርጅታችን በዘንድሮው የእንቁጣጣሽ በዓል ላይ በእጅ የተሳሉ የአደይ አበባ ሥዕሎችን በፍጥነት እና በጥራት የሚያከፋፍል "አበባ አዟሪ" ይፈልጋል። ይህ የሥራ ድርሻ ከፍተኛ ፍጥነትን፣ በወረቀት የተሳሉ ስዕሎችን ከክረምት ዝናብ እና ጭቃ ታድጎ ለደንበኞች ማድረስን እና አዋጭ እና አትራፊ ክፍያ መሰብሰብን ይጠይቃል።

የስራ መስፈርቶች

የትምህርት ደረጃ፡

  • በማንኛውም የትምህርት መስክ ዲፕሎማ ያለው/ላት

የስራ ልምድ፡

  • 0 ዓመት

  • በተመሳሳይ የሥራ መስክ ልምድ ያለው/ላት ቢሆን ይመረጣል

ብዛት፡ 5

የቅጥር ሁኔታ፦ የአጭር ጊዜ ኮንትራት (መስከረም 1 እና 2)

የሥራ ቦታ፦ አዲስ አባባ

ዋና ዋና ኃላፊነቶች፦

  • በA4 ወረቀትና ባለቀለም ማርከሮች የተሳሉ የእንቁጣጣሽ ስዕሎችን በብዛት መሳል፣ ማደራጀትና በአግባቡ መያዝ

  • የአደይ አበባ ሥዕሎችን ለደንበኞች በማስተዋወቅ የቤት ለቤት ሽያጭ ማከናወን

  • የተመረጡ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ለመድረስ የአካባቢውን መንገዶች በብቃት መጠቀም

  • ስዕሎቹ እንዳይጨማደዱ፣ ቀለማቸው እንዳይበላሽ እና በዝናብና በጭቃ እንዳይበከሉ በጥንቃቄ ማጓጓዝና መጠበቅ

  • ተገቢ የዋጋ ድርድር በማድረግ ለስዕሎቹ ተመጣጣኝ ክፍያ ማስገኘት

  • የአካባቢውን የተጨናነቁ መንገዶችና የትራፊክ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ በመመልከት በደህንነት ስራን ማከናወን

  • ከቡድን አባላት ጋር በመተባበር በቂ የሆኑ አዳዲስ ስዕሎች ማዘጋጀት

ክህሎቶች

  • የሥዕል ጥበብ ክህሎት፦ የአደይ አበባ ሥዕሎችን በፍጥነት፣ በጥራት እና በብዛት የመሳል ችሎታ

  • የአካል ብቃት፦ አጭር ርቀቶችን በቀላሉ የመንቀሳቀስ ችሎታ

  • የግንኙነትና የድርድር ችሎታ፦ ከሰዎች ጋር በአክብሮት የመግባባትና የመደራደር ችሎታ

  • የንብረት ጥበቃ ችሎታ፦ የወረቀት ስዕሎችን ከዝናብ፣ ከጭቃ፣ ከመጨማደድና ከመቀደድ በጥንቃቄ የመጠበቅ ችሎታ

  • የአካባቢ እውቀት፦ የሰፈሩን መንገዶች፣ አቋራጮችና ተመራጭ የስርጭት አካባቢዎችን በደንብ ማወቅ

  • የሥራ ጫናን የመቋቋም ችሎታ፦ በተጨናነቀና ፈጣን የሥራ ሁኔታ ውስጥ ተረጋግቶና በትኩረት መሥራት የሚችል

የማመልከቻ መመሪያ

አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ

Job Requirements በማንኛውም የትምህርት መስክ ዲፕሎማ ያለው/ላት አግባብነት ካለው የስራ ልምድ ጋር ዋና ዋና ኃላፊነቶች፦ - በA4 ወረቀትና ባለቀለም ማርከሮች የተሳሉ የእንቁጣጣሽ ስዕሎችን በብዛት መሳል፣ ማደራጀትና በአግባቡ መያዝ - የአደይ አበባ ሥዕሎችን ለደንበኞች በማስተዋወቅ የቤት ለቤት ሽያጭ ማከናወን - የተመረጡ ቦታዎች ላይ በፍጥነት ለመድረስ የአካባቢውን መንገዶች በብቃት መጠቀም - ስዕሎቹ እንዳይጨማደዱ፣ ቀለማቸው እንዳይበላሽ እና በዝናብና በጭቃ እንዳይበከሉ በጥንቃቄ ማጓጓዝና መጠበቅ - ተገቢ የዋጋ ድርድር በማድረግ ለስዕሎቹ ተመጣጣኝ ክፍያ ማስገኘት - የአካባቢውን የተጨናነቁ መንገዶችና የትራፊክ ሁኔታዎችን በጥንቃቄ በመመልከት በደህንነት ስራን ማከናወን - ከቡድን አባላት ጋር በመተባበር በቂ የሆኑ አዳዲስ ስዕሎች ማዘጋጀት How to Apply አመልክት/ቺ የሚለውን ይጫኑ

Deadline: Sep 10, 2026, 12:00 AM

Location:

Amount: 5